nnnnn

ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ማን ናቸው?

.................................................ከሥርጉተ ሥላሴ - ግንቦት 2000 ዓ.ም.

 

 

ልጆች እንደምን አላችሁ ? መቼም ተስፋ አለን አናንተም እንደ መምሪያው ስያሜ በእርግጥም  የሎሬት ተስፋ እንደምትሆኑ አይደል ? የኛ የዓይን አበባዎች ::  ለመሆኑ ልጆች ሎሬት ማን ናቸው ? ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን ኢትዮጵያዊ የጥበብ አባት ናቸው::

ልጆች ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሥነ ጽሑፍ ምሁር ናቸው:: የእርሳቸው የጥበብ የዕውቀት ደረጃ ከፍ ያለ በመሆኑ ሎሬት የሚለው የክብር ስም ተሰጥቷቸዋል::

 ሌላም ተጨማሪ የክብር ስም አላቸው:-

ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን ፀሐፊ፣ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ባለ ቅኔ እና ተርጓሚ የነበሩ የኢትዮጵያ የሀገራችን ልዩ ወርቅ፣ ዘውድ፣ ሀውልት ናቸው:: አሁን ግን ልጆች በሕይወት የሉም:: የካቲት 16 ቀን 1998 ዓ.ም* ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::

ነገር ግን ልጆች ሥራቸውና ሥማቸው ምንግዜም ከመቃብር በላይ ነው::ማለትም ያስተምረናል አሁንም ያስተምረናል:: ነገም ያስተምረናል:: ምንጊዜም ያስተምረናል::እና ልጆች እናንተም ጥበብ፣ ተፈጥሮአችሁም

የመድኀኒዓለም ጥበብ በመሆናችሁ በተጨማሪም


የአዲሱ ዘመን የ21ኛው መቶ ምዕተ ዓመትም ተረካቢ ተስፋዎች እናንተ ናችሁና የእናንተ መምሪያ የሎሬት ተስፋ ተባለ:: እንደ ድህረ ገጹ አዘጋጆች ፍላጎትና ምኞት የነገ ተስፋዎች እናንተ በጥበብ ውስጥ አንድትኖሩ፣ እንድታድጉ፣ ሕይወታችሁን በጥበብ እንድትመሩ እንፈልጋለን:: ከእናንተ ውስጥ ፀሐፊዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ደራሲዎች፣ገጣሚዎች፣ ተርጓሚዎች፣ አንባቢዎች፣ ተቺዎች፣የተውኔት ባለሙያዎች በሺህ ሳይሆን በሚሊዮን ንዲኖሩ መድኀኒዓለምን እንጠይቃለን::


ሰው ጥበብ ካረፈበት ሙሉ ሰውና ብቁ ዜጋ ይሆናል:: ብቁ ዜግነት ደግሞ ትውልዳዊ ድርሻ መክሊት ያመነጫል:: የእኛ ምኞት ይኽ ነው ልጆች::እናንተ የኢትዮጵያ ጌጥ፣ ልዩ ፈርጥ እና የደስታ ምንጭ ናችሁ::

ተስፋ ለተስፋ በተስፋ የተጀመረ ስለሆነ ተከታትላችሁ ታነቡ ዘንድ፣ እንዲሁም ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ ዓምዳችሁን ታሳድጉም ዘንድ አዘጋጆች ጥሪ እናቀርብላቸዋለን::

እሺ - የእኛ - ፈርጦች ! ! !

 

*በድምፅ / Audio Voice /  ላይ 1999 ዓ.ም. የተባለው በ1998 ዓ.ም. ተብሎ ይስተካከልልን:: ከይቅርታ ጋር!!!

 

 

<<Back to yeloret tesfa << Back to Menu        write your Comments