!    

            የምን መጪ፣ የምን ውጭ ? !

          

        መታሰቢያነቱ ለሐምሌ 13 ቀን 1999 ዓ. ም.

 

                    ከሥርጉተ ሥላሴ

                                             ግንቦት 2000 ዓ.ም.

በገርዳሜ- በወል- ፈታ

በሀገር- ፈት፤ በአውታታ

በቃለ ዓባይ፤ በወስላታ

እውነት እንዲህ ይመታ?

ሀቅ እንዲህ ተምታታ !

     አዬ ጊዜ?

ፍትህ በአሉታ ተመታ::

     እውነት በሀሰት ማግ - ተጠልፋ

             ሀቅ ማቅቃ - ተጣልፋ

     ሚዛን በእኩይ ተገፍታ

     እኮ ርትህ እንዲህ በበቀል ተወግታ !

       ምህረት በአባይ - ይቅርታ !

        በዕብለት - ኩፍኝ ተገርታ::

      ውሽት - ሹርባ ተሰርታ

      ቅጥፈት - ምላሷን ተበስታ

    ፍርድ መንምና - ከስታ


ሀቅ በመደዴ - ገርጥታ

ፍትህ ሀቅን ተቀምታ

ሚዛን በበቀል ተበጥታ::

በፈላጭ ቆራጭ ድንፋታ

በዘመነ ሄድሮስ ፍንዳታ

እውነት ለእውነት ፤ በዕብለት በግንባሯ ተደፍታ

ህዝበ መክሊት ተንጋላታ

ሚዛን ከ’ አግባብ ተዳፍታ::

        

  በነሸንግል በነተርታ . . .

        . . . በነ ቶፌ ተናግታ::

            በቃል አባይ - በአምታታ

         በቀጣፊ - በወስላታ::

     . . . ከአያ መለቲ- ተጣብታ

       ከጎሳ ጋር ተጋብታ::

      በቋሳ - ትውከት - በሁካታ

     የሀቅ ግድያ፤ ግንቦተ - ፍንዳታ::

 

 

 

ግንቦት 7- 97 ተንገላታ

የዲሞክራሲ ፏፏቴ ተገታ::

    ቀ - ና

ሕዝበ ድምፅ ቀና እንዳትል ተቀጥታ

ታሪክ ምስክር ፊት ተነስታ

እኮ፧እኮ በዕብለት ሀገር ሊፈታ ?

ታሪክ ለታሪክ

ይናገራል በእንብርክክ::

የክህደት - ጠኔ

በጎሳ - ጠመኔ

ይላል ወይኔ ቀኔ::

ይልስ ይሆን ቀኔ ?

ቀና - ቀኔ ፤ ቅንቅኔ ?

 

     ያኔ - አዎን - ያኔ

          ያኔ - ውይ - ያኔ

       ዕብለት - ያምላል

      . . .ይማማላል::

          አጋፋሪው ይከሳስላል

     ሆደ አምላኩም ይከሳስራል

        የቀን ጅቡም ይታወራል::

           ይላል ሸሸጉኝ ወሸቁኝ

          ክህደተ ሥንቁን ፤ የሙጥኝ::

 

ቀን - ሆይ - ሆይ - ሆይ

ቀና ቀንሽን ሳታወጪ አትሸሽጊ

መቅረዙን ይዘሽ ...

እባክሺ - እባክሺ - ሺ - ሺ - ሺ

ለ’ ሺ ለዕልፍሺ አንጊ !

ወንበዴን ክደሽ አንጋጊ:-

ፅናትን መቀነት አትዘንጊ::

 

           እውነትን አታንዘግዝ - ጊ

           አሽዋ አፍቅረሽ አታዛ - ጊ

           ማ’ ተመ ፍቅርን አትዘንጊ::

 

      ልብ:- ሆይ - ሆይ - ሆይ !

    መዝግቢ

     የትዕግስትን ሀቅ አገናዝቢ

     ለባለ ጊዜ አታራግቢ

     እኛንም አብረሽ አታንገርግቢ፣

             ለዕውነት መህለቅ ተንገብገቢ::

>> Continue to the Next Page2

 

Back to maedot<< Back to Menu        write your Comments