ር ዕ ስ አ ን ቀ ጽ

 

ማ ዕ ዶ ት

ከሥርጉተ ሥላሴ ግንቦት 2000 ዓ. ም.

ተስፋ - ቅኔ

ተስፋ - ቃና

ተስፋ - ቅኝት ነው::

 

የፍቅር ማዕዶት ፤

የዕውነት ማዕዶት ፤

የፍጥረተ ሰብዕ ማዕዶት፣

የትህትና ማዕዶት፤

የባህል ማዕዶት፣

የአንድነት ማዕዶት

የዕምነት ማዕዶት፤

የትውፊት ማዕዶት፤

ሁለንትና ኢትዮጵያ::

 

የአብሮነት ማዕዶት፤

የመከባበር ማዕዶት፤

የልዩ ታሪክ ማዕዶት፤

የይሉኝታ ማዕዶት፤

የጀግንነት ማዕዶት፤

የአትንኩኝ ባይነት ማዕዶት፤

ሁልዬ ኢትዮጵያ::

 

የውበት ማዕዶት፤

የ13 ወራት የፀሐይ ብርሀን ማዕዶት፤

የደመ ግቡነት ማዕዶት፤

የቃል ኪዳን ማዕዶት፤

የማተብ ማዕዶት፤

የጤና አዳም ማዕዶት፤

ውቢት ኢትዮጵያ::

 

የፀሎት ማዕዶት፤

የምስጋና ማዕዶት፤

የመሀሌት ማዕዶት፤

የቅኔ ማዕዶት፤

የድጓ ማዕዶት፤

የዜማ ማዕዶት፤

የምስጋና ማዕዶት፤

የቅዳሴ ማዕዶት፤

ሀገረ እግዚአብሔር::

 

የዝማሬ ማዕዶት፣

የወረብ ማዕዶት፤

የሰዓታት ማዕዶት፣

የገድላት ማዕዶት፤

የስግደት ማዕዶት፤

የንባብ ማዕዶት፤

የሱባኤ ማዕዶት፤

ጥበብ ኢትዮጵያ:-

 

እንጀራችን ክብ፣ መጋገሪያው ክብ፣

ሰቤጤራው ክብ፣- ድሆኖው ክብ፣

ሞግዱም ክበ፣ ሠፌዱ ክብ፣

ጎታው ክብ፣ ወራንታው ክብ፣

ገበታው ክብ፣ ግሬራው ክብ፣

ዓውድማው ክብ፣ ጎጆውም ክብ፣

ሞሰቡ ክብ፣ አከንባሎው ክብ፣

ድስቱ ክብ፣ ሙቀጫው ክብ፣

ቤተ እግዚአብሔሩ ክብ፣

ውሎአችን ክብ:-አቀማመጣችን ክብ፣

ሁሉም ክብ:-ክብብ:-

እጅግ በጣም ጥልቅ ትርጉም

ያላት ፍፁምተ ሀገር::

 

የአብሮነታችን የመተሳሰባችን፤

የመተሳሰራችን ማውጫ / ካታሎግ /

ማሳያ - መስታወት:: ማብራሪያ

( መዝገብ ) ማገናዘቢያ ( ምስክር )

ሰነዳችን ነው፡ ተዋህደን

የመኖራችን ልዩ ኢንሳይክሎፒዲያ:-

የታሪክ፣ የወግ፣ የባህል፣የዕምነት፣

ተቃቅፎ፣ ተዋህዶ፣ ተዋዶ

መኖርን የሚያመለክት፣ብቁ መረጃ::

ታዲያ ዓለም ኢትዮጵያ

የዓለም ሕዝብ መፈጠሪያ በሚልበት

በ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወያኔ

የዕድምታው ቅስም ሰባሪ ሆነ::

ያለታደለ አረም - አረማሞ አይደለም

የሕዝባችን ሥነ - ልቦና የሀገራችን እና

የቁሶቿ ሥነ- ተፈጥሮ

( የማይናገሩት - የማያናግሩት የጉዑዞቹ )

እንኳን ዓብይ ትርጉማቸው ጥልቅ ነው ፣ እጅግ::

 

ታዲያ የኢህአዴግ መራሹ መንግሥት ወያኔ አይደለም ለጉዑዙ፣ ነገር ለሰብዕናችን አብሮነት ሳያዝን በነቀዝ - እግዚአብሔር ይይለት ! አረመኔ። የሱ ማሳ የበደል አንበጣ አምራች ነው:: ይህ በደል ደግሞ በውስጥ ተፈጥሯአዊ ደም ላይ ያደማ ብቻ ሳይሆን ያቆሰለም ስለሆነ በዬትኛውም ዘመን ይሻራል ተብሎ ሊተነበይ የሚቻል አይመስለኝም:: እግዚአብሔር ረድቶን ወያኔ ቢጠፋ እንኳን የቁስሉ ቁርሾ ግን...እንጃ እኔ እንጃ... እሰተመቸ ብል ዲካውን መለካት ይሳነኛል::

 

>> Continue to page 2

 

Back to kana<< Back to Menu        write your Comments